አይ ጥበብ
Ay Tebeb
2005 · ትራክ 9 · 4:16 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይታየውንና የሚታየውን በሙሉ
በአንተ ተፈጠረ ይህ ሁሉ በሙሉ በሙሉ
በአንተ ተፈጠረ ሁሉ በሙሉ በሙሉ
ትርጉም አለው ሁሉም አስተውሎ ተመለከተው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉ በእርሱ ሆነ ያልሆነውስ አንዳች የቱ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ተወሰደ ልቤ በእሱኛው በእሱኛው
ሰው በሰራው ሳይሆን እግዚአብሔር በሰራው
ተማረከ ልቤ በእሱኛው በእሱኛው
በምድራዊው ሳይሆን በሠማያዊው ነው
አዝማች · Chorus
አይ ጥበብ ሆሆ
አይ ጥበብ (፬x)
አይሰራ አይ ጥበብ ረቂቅ ነው
በእርግጥ የማመልከው አምላክ ዕውቅታም ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የኮረብታውና የወንዙ የወፎች ጫጫታ
ጌታ በእጁ ብቻ ሳይሆን በቃሉ ብቻ ፈጠረ
በእጁ ሳይነካ በቃሉ ብቻ ፈጠረ
የውቂያኖስና የባሕር የጥልቀቱ
ትልቅ ነው ያሰኛል የጌታ አቤት ዕውቀቱ (፪x)
በሥራው በዕውቀቱ የተደነቀው
ፈጣሪውን ጌታ እኔ አመልከዋለሁ
የሁሉ የበላይ የበላይ የሆነው
እኔ የማመልከው እግዚአብሔር ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
አይ ጥበብ ሆሆ
አይ ጥበብ (፬x)
አይሰራ አይ ጥበብ ረቂቅ ነው
በእርግጥ የማመልከው አምላክ ዕውቅታም ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ