Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እስቲ ላነሳሳው

Esti Lanesasaw

2005 · ትራክ 11 · 5:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእርሱን ጥበብ ታላቅነት

ምስክር ነው የሰራው ፍጥረት (፪x)

ሁሉም ያውራ ይተርክለት

ቃሉን ሥራውን ይጨዋወቱት (፪x)

እኔስ ላውራለት

ቅኔን ልቀኝለት

ቅኔን ልቀኝለት (፪x)

እስቲ ላነሳሳው (፫x) እስቲ ልናገረው

የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው

ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው

አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (፪x)

የምድር ዕፅዋት የምድር እንስሳት

ለቅጽበት አይቆሙም ያለ አንተ ምህረት (፪x)

የአቀማመጥቸው አቤት የውበታቸው

ቢታቱ ቢታዩ የማይጠገቡ ናቸው (፪x)

አምልኮው ለአንተ

ዝማሬው ለአንተ

ዕልልታው ለአንተ

ጭብጨባው ለአንተ (፪x)

እስቲ ላነሳሳው (፫x) እስቲ ልናገረው

የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው

ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው

አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (፪x)

ሁሉን የሚችለው የአምላክ እስትንፋስ ፈጠረኝ

አበጃጀኝና ሕይወትንም ሰጠኝ (፪x)

የፈጠርከኝ ጌታ እኔም አከብርሃለው

ስለ አንተ ላወራ ይኸው መጥቻለሁ (፪x)

አምልኮው ለአንተ

ዝማሬው ለአንተ

ዕልልታው ለአንተ

ጭብጨባው ለአንተ (፪x)

እስቲ ላነሳሳው (፫x) እስቲ ልናገረው

የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው

ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው

አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (፪x)

አምልኮው ለአንተ

ዝማሬው ለአንተ

ዕልልታው ለአንተ

ጭብጨባው ለአንተ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ