አይጥልም
Aytelem
2010 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትዝ ይለኛል ትውስ ይለኛል
ለኔ ያደረግከው ከቶ አልረሳው
የማልችለውን እያስቻለኝ አቤት ስንቱን ቀን አሳለፈኝ
ተራራው ሸለቆው እንዳያደክመኝ በአባትነት ቃሉ እያባበለኝ
እያጽናናኝ (አሄሄሄ) በቤቱ አኖረኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
አይጥልም አይረሳም እግዚአብሔር ምስክር ነኝ እኔ
ከሰማሁት በላይ ሲያኖረኝ አይቻለሁ በዓይኔ (አሄ) (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
ያ ሁሉ መከራ በላዬ ያለፈ እስካይምስለኝ እንባዬ
እንዳለፈ ውሃ አለፈ ሃዘኔ ከኔ ተገፈፈ
እንዳለፈ ውሃ አለፈ (እንዳለፈ ውሃ አለፈ) (፬x)
እንዳለፈ ውሃ አለፈ (ሃዘኔ ከኔ ተገፈፈ) (፪x)
እንዳለፈ ውሃ መከራዬ አለፈ (፪x)
አለፈና አለፈና
ያልተፈጠሩት ቀናቶቼን ቀድሞ ሲያቀናልኝ መንገዴን
የልጅነቴ አምላክ እጣ ፈንታዬ እንደዘመርኩለት ሆኖኝ ካሳዬ
ተጽናናሁኝ (አሄሄሄ) ታብሶ ዕንባዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
አይጥልም አይረሳም እግዚአብሔር ምስክር ነኝ እኔ
ከሰማሁት በላይ ሲያኖረኝ አይቻለሁ በዓይኔ (አሄ) (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ