Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይገባዋል

Yegebawal

2010 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሰማይ ሰማያት ክብሩን ጥሎ መጥቶ

ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት መብቱን ሁሉ ትቶ

የማይገባውን ዋጋ ከፈለ

ኢየሱስ ኢየሱስ ግሩም ድንቅ ንጉሥ

አልፋና ኦሜጋ የይሁዳ አንበሳ

የሞት መውጊያን ሰብሮ ጥሎት ተነሳ

ይገባዋል ታርዷልና

ብዙ ክብር ምሥጋና

ድል ለነሳው የድል ዜማ

ፍጥረት ሁሉ እንዲሰማ (፪x)

ክብር ዝና ባለጠግነት

ለታረደው በግ ይሁንለት (፬x)

የቀራንዮ ስቃይ ያን ሁሉ መከራ

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ

ሲዘባበቱበት ሁሉም በተራ

ባህር ውቅያኖሱን የፈጠረ ጌታ

ተጠማሁኝ አለ ተሰቅሎ ጐልጐታ

የአዳምን ዘር ሊያድን ሞትን ሊገታ

ይገባዋል ታርዷልና

ብዙ ክብር ምሥጋና

ድል ለነሳው የድል ዜማ

ፍጥረት ሁሉ እንዲሰማ (፪x)

ክብር ዝና ባለጠግነት

ለታረደው በግ ይሁንለት (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ