Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምን ይለኛል

Men Yelegnal

2010 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

የሆነልኝ ነገር ሚስጥሩ ያልገባው (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

እኔስ እንደ ዳዊት እርቃኔን ባመልከው (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

ብዬስ አምልኮዬን ፈጽሞ አልቀንስም (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

የሆነልኝ ነገር ዝምም አያሰኝም (አዎ)

ያለውን ይበል እንጂ ያሻውን እንደልቡ

ያልገባው ያልተረዳው ቢተቸኝ እንደ ሃሳቡ

ከትቢያ ላይ ላነሳኝ ለክብሩ እዘምራለሁ

ከውርደቴ ላሰበኝ ለስሙ እቀኛለሁ (፪x)

የምስኪን ወዳጅ ለድሃደጉ

አባት ለሌለው ክብሩ ማዕረጉ

ያየ ይመስክር የማይረሳት ሰው

ያለፍኩበትን እኔስ አልረሳው

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው (፬x)

እንዴት እንደረዳኝ እኔ ነኝ የማውቀው

ከየት እንዳነሳኝ እኔ ነኝ የማውቀው (፪x)

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው (፪x)

ፍቅሩን ምህረቱን ቀምሼዋለሁ

እንደ ኢየሱሴማ የት አገኛለሁ

እድሜ ዘመኔን ለእርሱ ብዘምር

አልጨርሰውም ሁሉን ብናገር

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው (፬x)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

የሆነልኝ ነገር ሚስጥሩ ያልገባው (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

እኔስ እንደ ዳዊት እርቃኔን ባመልከው (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

ብዬስ አምልኮዬን ፈጽሞ አልቀንስም (አዎ)

ምን ይለኛል (ምን ይለኛል)

የሆነልኝ ነገር ዝምም አያሰኝም (አዎ)

ያለውን ይበል እንጂ ያሻውን እንደልቡ

ያልገባው ያልተረዳው ቢተቸኝ እንደ ሃሳቡ

ከትቢያ ላይ ላነሳኝ ለክብሩ እዘምራለሁ

ከውርደቴ ላሰበኝ ለስሙ እቀኛለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ