ክቡር ሆይ
Kebur Hoy
2010 · 5:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የተከሸኑ ቃላቶች አንተን አይገልጹህምና
ትልቅ ነህ ልበልህ ደግሜ
ትልቅ ነህ ልበልህ ገናና (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመስልህ ታጣ ቢፈለግ ቢፈለግ
በምድር ትልቁ እግዚአብሔር
የሚያክልህ ታጣ ቢፈለግ ቢፈልግ
በምድር ትልቁ እግዚአብሔር (፪x)
ክቡር ሆይ ክቡር ሆይ
ከብረህ ኑር ዘላለም
በከበረው ዙፋንህ ላይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቻና እኩያ ሳይኖርህ ብቻህን ትገዛለህ
የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ አንተ ለዘላለም ኗሪ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመስልህ ታጣ ቢፈለግ ቢፈለግ
በምድር ትልቁ እግዚአብሔር
የሚያክልህ ታጣ ቢፈለግ ቢፈልግ
በምድር ትልቁ እግዚአብሔር (፪x)
ክቡር ሆይ ክቡር ሆይ
ከብረህ ኑር ዘላለም
በከበረው ዙፋንህ ላይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚመስልህ ጠፋ (፪x) ቢፈለግ ቢፈለግ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚመስልህ ጠፋ ቢፈለግ ቢፈለግ
ትልቁ እግዚአብሔር (፪x)
የሚያክልህ ታጣ ቢፈለግ ቢፈልግ ትልቁ እግዚአብሔር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ