ተለመነን
Telemenen
2010 · 5:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተለመነን (፬x)
አምላካችን ፈጣሪያችንን
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ ጌታ ሆይ እስኪ ተለመነን
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዲሁ አንለፍ ክብርህን አሳየን (፪x)
በጮማና በስብ ስጋቸው ደልቦ
መንፈሳቸው ግን ከሳ ጽድቅን ተርቦ
የተመኙ አግኝተው ምድራዊውን ተድላ
ሲደሰቱ አላየንም ውስጣቸው ሲሞላ
መች ሆነና ሞገስ መልካም በለበሰ
ሰማያዊው ፀጋ ከላይ ካልፈሰሰ
እውነትና ምህረት የተገለጡለት
እሱ ነው ስጦታ እሱ ነው በረከት
አዝማች · Chorus
ተለመነን ኧኸ ኧኸ ተለመነን ኧኸኸን (፪x)
አቤቱ ጌታ ሆይ እስኪ ተለመነን
እንዲሁ አንለፍ ክብርህን አሳየን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብርና ዝናን በመቃብር ሊቀር
ኮበለለ ወገነ ሰው ከጨለማ ጋር
ቃዬል በአቤል ላይ ወንድም በወንድሙ
ሞትን ዘራ በዘሩ ይከሰዋል ደሙ
ወይ ዘመነ ምህረት ጻድቅ መንገድ ወድቆ
እግዚአብሔርን መፍራት ከትውልድ እርቆ
ኃጥ ሲለመልም ፈራጅ እንደሌለ
ከልካይ ሆይ ተነሳ ብሎ ይኸው አለ
አዝማች · Chorus
ተለመነን ኧኸ ኧኸ ተለመነን ኧኸኸን (፪x)
አቤቱ ጌታ ሆይ እስኪ ተለመነን
እንዲሁ አንለፍ ክብርህን አሳየን (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ተለመነን ኧኸ ኧኸ ተለመነን ኧኸኸን (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ