Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ገና ከጅምሩ

Gena Kejemeru

2010 · 5:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ገና ከጅምሩ ውድቀቴን ሲጠባበቁ

በትንሽ በትልቁ ድካሜ ሲሳለቁ (፪x)

ልቤ በጌታ ላይ አበረታሁና

ዛሬ ከፍታ ላይ ወጣሁ ለምሥጋና (፪x)

ጅማሬዬ ታናሽ ቢመስል ፍፃሜዬ የአማረ ነው

ያለኝን ጌታ ሰምቼ በቤቱ ፀንቻለሁ

ሟርተኞች የሟረቱ ስንቶች ተነስተው ቢሞቱ

የጠራኝ የቀባኝ ጌታ አይጥለኝ ለአፍታ

ከሳሼ ያልገባው አንድ ነገር

አባቴ መሆኑን እግዚአብሔር

ሊከሰኝ ቢፈልግ ፍርድ የእኔ ነው

ይህን እንኳን የማያቅ ምኑ ሞኝ ነው (፪x)

ገና ከጅምሩ ውድቀቴን ሲጠባበቁ

በትንሽ በትልቁ ድካሜ ሲሳለቁ (፪x)

ልቤ በጌታ ላይ አበረታሁና

ዛሬ ከፍታ ላይ ወጣሁ ለምሥጋና (፪x)

የማያልፍ የመሰለኝ ያ ዘመን ካለፈልኝ

ነገንም በእርሱ ላይ ጥዬ ልዘምር ተደላድዬ

አቤኔዘር ሆኖኛልና ልጨምር ብዙ ምሥጋና

ለረዳኝ ላገዘኝ ጌታ ለሆነኝ እድል ፈንታ

ከሳሼ ያልገባው አንድ ነገር

አባቴ መሆኑን እግዚአብሔር

ሊከሰኝ ቢፈልግ ፍርድ የእኔ ነው

ይህን እንኳን የማያቅ ምኑ ሞኝ ነው (፪x)

ገና ከጅምሩ ውድቀቴን ሲጠባበቁ

በትንሽ በትልቁ ድካሜ ሲሳለቁ (፪x)

ልቤ በጌታ ላይ አበረታሁና

ዛሬ ከፍታ ላይ ወጣሁ ለምሥጋና (፪x)

ከሳሼ ያልገባው አንድ ነገር

አባቴ መሆኑን እግዚአብሔር

ሊከሰኝ ቢፈልግ ፍርድ የእኔ ነው

ይህን እንኳን የማያቅ ምኑ ሞኝ ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ