ማረን
Maren
2010 · 6:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማረና አባት ሆይ ማረና
ማረና አሁንም ማረና
ማረና አመጻችን በዝቶን
ማረና ደካክመናልና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሳናውቅ በስህተት ከሰራነው ይልቅ
የድፍረት ኃጢአታችን በዛ
አሁንስ ፈርተናል እጅግ ተጨንቀናል
በፊትህ ለመቆም አቅም የለንምና
ማረና
አዝማች · Chorus
ማረና አባት ሆይ ማረና
ማረና አሁንም ማረና
ማረና አመጻችን በዝቶን
ማረና ደካክመናልና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የቆምን ሲመስለን ያለንበት ከፍታ
በኃጢአት ተጠምደን ታስረን ሳንፈታ
በሰው ፊት ሙሉ ነን አልጐደለብንም
ጓዳችን ሲፈተሽ ከአንተ ጋር የለንም
ማረና
አዝማች · Chorus
ማረና አባት ሆይ ማረና
ማረና አሁንም ማረና
ማረና አመጻችን በዝቶን
ማረና ደካክመናልና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስኪ ማረን ተቀበለን
ከአንተ ውጪ ማንም የለን
አባ ማረን ተቀበለን
ከአንተ ውጪ ማንም የለን (፭x)
አዝማች · Chorus
ማረና አባት ሆይ ማረና
ማረና አሁንም ማረና
ማረና አመጻችን በዝቶን
ማረና ደካክመናልና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ