Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዛሬማ

Zariema

2010 · 4:57 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሁን ገና ገባኝ ገና እንዴት እንዳለፍኩት

ያንን የጭንቅ ቀን ዞር ብዬ አየሁት

ማስተዋል አግኝቼም አይደል ጥበብን ተክኜ

እንዲህ ነው አልልም እንደሰው እራሴን ታምኜ

ለካስ ስለረዳኝ ስላገዘኝ እንጂ

ያ የእኔ ወዳጅ (፪x)

ማን ያስበኝ ነበር ማን ያነሳኝ ነበር

ከመቅደሱ ደጅ ከመቅደሱ ደጅ (፪x)

ዘልቄ እንዳልገባ አልፌ የሚታይ ምንም የለም

ሞገስ አገኘሁኝ በአምላኬ ጸሎቴም ተሰማልኝ

ዛሬማ ቀና ብያለሁ ዛሬማ ሁሉ ተረስቶ

ዛሬማ ንጉሠ ነገሥት ዛሬማ ከቤቴ ገብቶ

ዛሬማ ቀና ብያለሁ ዛሬማ ሁሉ ተረስቶ

ዛሬማ የጌቶች ጌታ ዛሬማ ከቤቴ ገብቶ (፪x)

አሁን ገና ገባኝ ገና እንዴት እንዳለፍኩት

ያንን የጭንቅ ቀን ዞር ብዬ አየሁት

ማስተዋል አግኝቼም አይደል ጥበብን ተክኜ

እንዲህ ነው አልልም እንደሰው እራሴን ታምኜ

ለካስ ስለረዳኝ ስላገዘኝ እንጂ

ያ የእኔ ወዳጅ (፪x)

ማን ያስበኝ ነበር ማን ያነሳኝ ነበር

ከመቅደሱ ደጅ ከመቅደሱ ደጅ (፪x)

ሰው እንዲያይ ፊት አይቶ አይፈርድም ልብን ይመረምራል

በጊዜው ነገሬን ውብ አርጐ ታሪኬን ቀይሮታል

ዛሬማ ቀና ብያለሁ ዛሬማ ሁሉ ተረስቶ

ዛሬማ ንጉሠ ነገሥት ዛሬማ ከቤቴ ገብቶ

ዛሬማ ቀና ብያለሁ ዛሬማ ሁሉ ተረስቶ

ዛሬማ የጌቶች ጌታ ዛሬማ ከቤቴ ገብቶ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ