አይወስንህ ሁኔታ
Ayweseneh Hunieta
2006 · ትራክ 6 · 4:45 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ
በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ
አይወስንህ ሁኔታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሠማይ በታች ፍጥረት የሚያገኘው
ደስታው የማይጸና የከንቱ ከንቱ ነው
ታዲያ ምብዛቱ ጥቅሙ ምንድን ነው
ምኞቱ መሻቱ ንፋስ መከተሉ
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ
በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ
አይወስንህ ሁኔታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የዚች ዓለም ውብት መቼ ደስታ ይሰጣል
ትናንት የነበረ ድንገት ከእጅ ያመልጣል
ቋሚ ነገር የለም ለሁሉም ጊዜ አለው
የሚጸና ደስታ እግዚአብሔር ብቻ ነው
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ
በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ
አይወስንህ ሁኔታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መብዛትን መጉደልን ሁሉ ተምሬያለሁ
ኃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ
ነገር ተለዋዋጭ መሆኑን አየሁኝ
የሚጸና ደስታ ጌታን አገኘሁኝ
ደስታዬ አንተ ብቻ
ሰላሜ አንተ ብቻ
እረፍቴ አንተ ብቻ
ሃብቴ አንተ ብቻ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ
በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ
አይወስንህ ሁኔታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ