እኔም አምነዋለሁ
Eniem Amnewalehu
2006 · ትራክ 8 · 4:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የገባልኝን ቃል እስከሚፈፅመው
እግዚአብሔር ይተጋል
እኔም አምነዋለሁ (፬x)
የገባልኝን ቃል እስከሚፈፅመው
እግዚአብሔር ይተጋል
እኔም አምነዋለሁ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍፁም የማይገባ የማይመስል ነገር
እንደምን ይሆናል የተባለ ቢሆን
የአብርሃም አምላክ በቃሉ የታመነ
እውን ያደርገዋል ተስፋ ከእርሱ ካለ
ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ
እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቀናቶች ቢረዝሙ ችግሩም ቢበዛ
እምነቴም ቢፈተን ጠላትም ቢነሳ
ቃል ተናግሯልና ይሆናል አይቀርም
ጌታዬ ሲከፍተው ማንም አይዘጋውም
ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ
እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓይኖቹ ያዩኛል ጆሮውም ይሰማኛል
የልቤን ጥያቄ ጌታዬ ያውቀዋል
መልስ እስከሚመጣ እስከሚጐበኘኝ
አፅንቶ የሚያቆም የተስፋ ቃል አለኝ
ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ
እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ