ክቡር ነው
Kebur New
2006 · ትራክ 3 · 4:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በአንተ የተደነቀ ምህረት የበዛለት
ምስግናን ያመጣል ፍቅሩን ሊገልጽበት
ዘመኑን በሙሉ ቢቀኙ ለክብርህ
ከመታወቅ ያልፋል የአንተስ ማንንነት
ዝማሬው ቢበዛ ቢጨማምርለት
ምሥጋናው ቢበዛ ቢጨማምርለት
አድንቆት ቢበዛ ቢጨማምርለት
የቱም አይገልጸዉ የእርሱን የእርሱን ታላቅነት
የቱም አይገልጸዉ የእርሱን ኃያልነት
አዝማች · Chorus
ክቡር ነው የከበረ በክብር የተሞላ
ድንቅ ነው የሚደነቅ በኃይል በሥራ (፪x)
እግዚአብሔር የሚወደድ እግዚአብሔር የሚፈራ
እግዚአብሔር የሚደነቅ እግዚአብሔር የሚያኮራ
አምላኬ አንተ ልዩ ነህ የቱ ዝማሬ ይገልጽሃል (፪x)
ጌታዬ አንተ ልዩ ነህ የቱ ምሥጋና ይገልጽሃል (፪x)
አባቴ አንተ ልዩ ነህ የቱ ምሥጋና ይገልጽሃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኦሆሆ አሃሃ (፬x)
ላስተዋለውማ ሆሆ ፀጋው ለበዛለት
ንቆ ይህን ዓለም አሃ የሚጠፋውን እውነት
በእምነት እያየው ፊትህን እለት እለት ኦሆ
እንዴት ደስ ያሰኛል ለክብርህ መቀኘት (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦሆሆ አሃሃ (፬x)
ክቡር ነው የከበረ በክብር የተሞላ
ድንቅ ነው የሚደነቅ በኃይል በሥራ (፪x)
እግዚአብሔር የሚወደድ እግዚአብሔር የሚፈራ
እግዚአብሔር የሚደነቅ እግዚአብሔር የሚያኮራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ