እግዚአብሔር ሲሰራ
Egziabhier Sisera
2006 · ትራክ 5 · 3:55 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአፌ የወጣው ቃል ምንም ሳያፈራ
ከቶ አይመለስም ሥራውን ሳይሰራ [1]
ብሎ የተናገረው ለሥሙ የሚቀና
ገና አሁን እናያለን እግዚአብሔር ሲሰራ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደነቃልን እንደነቃልን
እግዚአብሔር ሲሰራ በዓይናችን እያየን (፪x)
በዓይናችን እያየን (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይህ እንዴት ይሆናል ማንስ ያውቅበታል
ያስ እንደምን ሆኖ ወደዚህ ይደርሳል
በመንፈሱ እንጂ በኃይል የማይሆነው
የእግዚአብሔር ሥራ ሁሌም ፍጻሜ አለው (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደነቃልን እንደነቃልን
እግዚአብሔር ሲሰራ በዓይናችን እያየን (፪x)
በዓይናችን እያየን (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር የሚያስመካ
የሚያስደንቅ የሚያኮራ
ሥራው ድንቅ ነው ሲሰራ
ሥራው ልዩ ነው ሲሰራ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚታመን በአንተ ይታመን
የሚመካ በአንተ ይመካ
የሚደገፍ በአንተ ይደገፍ
የሚኮራ በአንተ ይኩራ
ቁጥር 5 · Verse 5
እኛስ ኩራት ኩራት ይለናል ይለናል (፪x)
በአንተ መደገፉ ያስመካናል (፪x)
የአንተ መሆናችን ያስመካናል (፪x)
እኛስ ኩራት ኩራት ይለናል ይለናል (፪x)
በአንተ መደገፉ ያስመካናል (፪x)
በአንተ መታየቱ ያስመካናል (፪x)
በአንተ መደገፉ ያስመካናል (፪x)
በአንተ መታየቱ ያስመካናል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ