ልባርክህ
Lebarkeh
2006 · ትራክ 4 · 4:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ባከብርህ ባመልክህ ባመሰግንህ
ተባረክ ተወደስ ክበር እያልኩህ
መቼ ይበቃኛል አንተን ሊገልጽህ
ለእኔ ታደረከው ጌታ እየበዛብኝ
በተከፋሁ ጊዜ ልቤ ሃዘን ሲውጠኝ
አንተ ብቻ ለእኔ ፈጥነህ ደረስክልኝ
ከእኔ ጋራ ሆነህ ነፍሴን እያጽናናህ
ያንን ጨለማዬን በብርሃንህ አበራህ
ስለዚህ ጌታዬ ወዳጄና አባቴ
ወዴት እሄዳለሁ ይህን ፍቅር ትቼ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በፊትህ ስበድል በአመጼ ስትቀጣኝ
በበደሌ አዝኜ ፊትህን ላይ ስመኝ
አይተህ አዘንክልኝ በንስሃ ሞልተህ
ጽድቅን አወጣሃት ጠላቴን ረግጠህ
ድካሜ ቢበዛ ጉድለቴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ሙላቴ
እንዲሁ በፀጋህ ቆሜያለሁ
ሥምህን በዜማ አከብራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይገርመኛል ይሄ ፀጋ
ይደንቀኛል ይሄ ፀጋ (፪x)
የዳንኩበት ይሄ ፀጋ
የቆምኩበት ይሄ ፀጋ
የሚያጽናናኝ ይሄ ፀጋ
የሚያስኬደኝ ሃሌሉያ
ቁጥር 3 · Verse 3
ድካሜ ቢበዛ ጉድለቴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ሙላቴ
እንዲሁ በፀጋህ ቆሜያለሁ
ሥምህን በዜማ አከብራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይገርመኛል ይሄ ፀጋ
ይደንቀኛል ይሄ ፀጋ (፪x)
የዳንኩበት ይሄ ፀጋ
የቆምኩበት ይሄ ፀጋ
የሚያጽናናኝ ይሄ ፀጋ
የሚያስኬደኝ ሃሌሉያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ