Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅር ነው

Feqer New

2006 · ትራክ 7 · 4:32 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለ ሰው ልጅ ነፍሱን አሳልፎ

እስከ መስቀል ታዟል እራሱን አዋርዶ

እንዲህ ያለ መውደድ ከወዴት ተሰምቷል?

በእግዚአብሔር አብ ፍቃድ በኢየሱስ ተገልጧል (፪x)

ፍቅር ነው ጌታ ፍቅር ነው

ስራው ፍቅር ነው ስሙ ፍቅር ነው (፪x)

የኃያላን ጉልበት ዝናው ሁሉ ያልፋል

ክብሩ ከበሬታው ከንቱ ነው ይቀራል

የእኛ ኢየሱስ በግርማ በክብር

በኃይል በሞገሱ ፀንቶ የሚኖር (፪x)

ኃያል ነው ጌታ ኃያል ነው

ስራው ኃያል ነው ስሙ ኃያል ነው

ፊት አይቶ አያደላ ለሁሉ ነው ወዳጅ

የልብ ን የሚረዳ እውነተኛ ፈራጅ

ስራው በትክክል ሚዛኑ እውነት ነው

በዘመናት ሁሉ በስራው ፃድቅ ነው (፪x)

ፃድቅ ነው ጌታ ፃድቅ ነው

ስራው ፃድቅ ነው ስሙ ፃድቅ ነው (፪x)

ሌላ ምን እንበልህ ምን እናቅርብ

በፊትህ ከማዜም ከመቀኘት በቀር (፬x)

ለአንተ ነው እንጂ ይኸው ዝማሬ አምልኮ

ስግደት ዕልልታ ክብር አሜን ይሁን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ