ማራናታ
Maranatha
2006 · ትራክ 2 · 5:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ
በእኔም ደግሞ እመኑ ፤
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ፤
እንዲህስ ባይሆን ባልኋቹ ነበር
ስፍራ አዘጋችላቹህ ዘንድ እሄዳለሁና ፤
ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ
ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ
ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ"
ቁጥር 2 · Verse 2
ያስጨነቀንን ሁሉ ደግመን ልናስበው
እንባችንን ሊያብስ ሃዘንን ሊያርቀው
ይህንን ፈራሽ ሥጋ በክብር ሊለውጠው
ቀን ቀጥሯል እግዚአብሔር ቃሉን ሊፈጽመው
አዝማች · Chorus
ይመጣል ጌታ ይመጣል
ይመጣል ኢየሱስ ይመጣል
ይመጣል በክብር ይመጣል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላት ጦር አውጥቶ ቢያጥር ዙሪያችንን
ኑሮው ትግል ሆኖ ቢያዝል ቢያደክመን
የጠበቅነው ኢየሱስ በክብር ሲመጣልን
እኛም ከእርሱ ጋር አብረን እንከብራለን
አዝማች · Chorus
ይመጣል ጌታ ይመጣል
ይመጣል ኢየሱስ ይመጣል
ይመጣል በክብር ይመጣል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር መለከት ከሠማይ ይወርዳል
የወጉትም ሁሉ በዓይናቸው ያዩታል
በሙታን ሕያው ላይ ሊፈርድ ይገለጣል
የጌታ ምጻቱ ጊዜያቱ ተቃርቧል
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ ማራናታ
ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ቃሉን የሰጠን የታመነ ነው
በክብር በአብ ቀኝ የተቀመጠው
ወላጅ እንደሌለው ከቶ ላይተወን
ይመጣል ኢየሱስ ሃሌሉያ እኛን ሊወስደን (፪x)
አዝማች · Chorus
ማራናታ ማራናታ ማራናታ
ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ