Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መድኃኒቴ

Medhanitie

2006 · ትራክ 9 · 3:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እጅግ ከሚያስፈራው ከገሃነም እሳት

መድሃኒት የሆንከኝ ነፍሴን የታደካት

ወደ ውስጤ ገብተህ ፈውስን አግኝቻለሁ

ለዘለዓለሙ ሳልሰጋ እኖራለሁ (፪x)

መድሃኒቴ አንተ ነህ ኦሆሆ ሌላማ የለኝም አሃሃ

እውነተኛ አዳኝ ኦሆሆ ፈዋሽ የሆንከኝ አሃሃ

ሌላማ ሌላማ ሌላማ የለኝም (፪x)

ሃሌሉያ

መከራ ዙሪያዬን ሲያስፈራ ሲከበኝ

ቀር ቦ የነበረ ወዳጅም ሲሸሸኝ

ያለኝ የመሰለኝ ከጄ ሲጠፋብኝ

አልጥልሽም እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ አልከኝ (፪x)

መድሃኒቴ አንተ ነህ ኦሆሆ ሌላማ የለኝም አሃሃ

እውነተኛ አዳኝ ኦሆሆ ረዳት የሆንከኝ አሃሃ

ሌላማ ሌላማ ሌላማ የለኝም (፪x)

ሃሌሉያ

ዛሬም ወደፊት ለሚያስፈልገኝ

ማንስ ሊያበረታ ማንስ ሊያግዘኝ

ሰላምም መፍትሔም መሆን የሚቻለው

እውነተኛ ተስፋ ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)

መድሃኒቴ አንተ ነህ ኦሆሆ ሌላማ የለኝም አሃሃ

እውነተኛ አዳኝ ኦሆሆ ፈዋሽ የሆንከኝ አሃሃ

ሌላማ ሌላማ ሌላማ የለኝም (፪x)

ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ