ለክብሩ ዘምሩ
Lekebru Zemeru
2006 · ትራክ 12 · 4:17 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ
ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ
እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሠማያዊ ሚስጢር የገለጸላችሁ
ከድቅድቅ ጨለማ መጥቶ ያወጣችሁ
ይህን እግዚአብሔርን እስኪ እናመስግነው
በዝማሬ ዕልልታ ክበር እንበለው
አዝማች · Chorus
ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ
ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ
እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የምድር ሁሉ ደስታ የፅዮን ተራራ
እግዚአብሔር ጥልቅ ነው ክብሩ የሚያስፈራ
እንደ እርሱ ያለ አምላክ ከቶ ስላላየን
ለታላቁ ጌታ እንሰግድለታለን
አዝማች · Chorus
ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ
ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ
እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አዲስን ዝማሬ ለእርሱ ዘምሩ
ታላቅነቱንም ግርማውንም አውሩ
ክብሩን ለአሕዛብ እንናገራለን
ተዓምራቱን ደግሞ እኛ እናወራለን
አዝማች · Chorus
ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ
ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ
እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የእርሱን በጐነት መልካምነቱን
ማለዳ ማለዳ ምሕረቱን ካየን
በፀጋው በፍቅሩ ጠብቆ ላቆመን
ቆመን ከነፍሳችን ምሥጋና እንሰጣለን
አዝማች · Chorus
ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ
ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ
እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ