Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

Bado Sheleqon Yimolal

2005 · ትራክ 4 · 7:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

ምድረ በዳውን ያለመልማል

ነፋስ ዝናብ ባይኖርም

ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም (፪x)

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

የቤት የጓዳው መብል ተሟጦባቸው ድረስ ና ላሉት

በእንባ በጸሎታቸው እየጮሁ ለተማጸኑት

መንገድ አለው መላ በመልሱ የሚያሳርፍበት

የደረቀውን ኑሮ በቸርነቱ የሚያለመልምበት

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

ምድረ በዳውን ያለመልማል

ነፋስ ዝናብ ባይኖርም

ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

የቀጠረለትን ቀን ምስኪኑን የሚባርክበት

ይጠብቃል አውቀን ምን እንደተዘጋጀለት

ያያል እጁ ሲገባ ሲያቆምለት ያን የደም እንባ

የሱም ደሳሳ ጐጆ ሰው በማይንቅ አምላክ ታስባ

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

ምድረ በዳውን ያለመልማል

ነፋስ ዝናብ ባይኖርም

ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ድንጉጥ ልበ ፈሪዎች ለሰጉ ለተጠራጣሪዎች

ስለ ነገ ተጨንቀው የትላንቱን ተዓምር ለረሱ ሰዎች

መልዕክት አለው ዛሬም እኔ እኔ ነኝ አልተለወጥኩም

ይመስክሩ ልጆቼ ተስፋ ያረጉኝን አላሳፈርኩም

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

ምድረ በዳውን ያለመልማል

ነፋስ ዝናብ ባይኖርም

ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ቀንበር ለከበዳቸው የዚህ ዓለም ኑሮ ለመረራቸው

ቀኙን ግራውን ቢሉ ቢንከራተቱ ላልሞላላቸው

እንጀራ ላጡ እንጀራ ባርኮ ሰጥቶ ያቀርባችኋል

ብዙ ረሃባችሁን በብዙ ጥጋብ ይለውጥላችኋል

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ባዶ ሸለቆን ይሞላል

ምድረ በዳውን ያለመልማል

ነፋስ ዝናብ ባይኖርም

ተዓምር መስራቱ ፈፅሞ አይቀርም

ይችላል እግዚአብሔር ይችላል (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ