Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፀጋ እፈልጋለሁ

Tsega Efelegalehu

2005 · ትራክ 10 · 4:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ

ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (፪x)

ጉልበቴ ሳይላላ ሳይቀንስ ትጋቴ

በቤትህ መኖር ነው ሌት ተቀን መሻቴ

ልገስግስ ወደፊት እየታደሰ ኃይሌ

በመክሊቴ ላትርፍ ይብዛ ማገልገሌ

አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ

ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (፪x)

የድል አድራጊ ልጅ ባለ ድል አርገኸኝ

ሽንፈታም ነኝ እያልኩ ሳወራ እንዳልገኝ

የሰራህልኝን መልካሙን ሥራህን

እንዳልረሳው እርዳኝ ያንን ውለታህን

አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ

ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (፪x)

ፍጻሜዬን አሳምር እንደ ጅማሬዬ

በመልካም ይደምደም በፊትህ ሩጫዬ

ሁሉ በአንተ ከአንተ ለአንተ ነውና

ይኸው ክበርብኝ ዝቅ ልበልና

አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ

ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (፪x)

ለባዕድ አልሰጥም ይህን ጉብዝናዬን

ወስኛለሁ አጽናው ቅዱሱን ምርጫዬን

ልኑር እንደ ቃልህ ግራ ቀኙን ሳላይ

እስካገኝ ርስቴን እስክገባ ሰማይ

አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ

ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ