በእሳት ውስጥ
Besat West
2005 · ትራክ 7 · 5:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም
በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም
ቁጥር 1 · Verse 1
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (፪x)
ወጀቡን ተው አውሎ ነፋሱንም
እየገሰጸ ረዳኝ አልተወኝም
አሻገረኝ ወዲያ ወዲያ ማዶ
አልመሸብኝ መጥቶልኛል ማልዶ
አዝማች · Chorus
በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም
በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አብሮኝ ሲጓዝ ሜዳ ተራራውን
መቼም ቢሆን አልረሳም ውለታዉን
እያስቻለኝ ልቤን እያሰፋ
ደጋገፈኝ ያዘኝ እንዳልጠፋ
አዝማች · Chorus
በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም
በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤት ስንቱን ስንቱን አሳለፈኝ
እየከለለ ክፉ እንዳያገኘኝ
ጐኔ ባይቆም ለሁለ ባቄ ነኝ
ማዕበሉ ወጀቡ በከደነኝ
አዝማች · Chorus
በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም
በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አይዞህ ባዬ አጽናኜ ጌታዬ
የሰላም ምንጭ ደስታዬ እርካታዬ
ተወጣሁት ጉልበቴ ኃይል ሆኖ
አላፈረም ማንም እርሱን ተማምኖ
አዝማች · Chorus
በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም
በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም
እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ