Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተቀይሯል

Teqeyrual

2005 · ትራክ 2 · 5:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

ትርፉ ድካም ሁልጊዜ እሮሮ

ስቆ ማልቀስ የዚህ ዓለም ኑሮ

እዚም እዚያም ደስታ ለማግኘት

ገላገለኝ ከመንከራተት

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

አዋጥቶኛል እርሱን ማለቴ

እረፍት ሆነኝ ሰላም ለቤቴ

እጅ እግሬን የቆለፈ ኃጢያቴ

በጣጥሶታል እስራቴን

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

ሄድኩኝ በቃ ተከትየው

መድኃኒቴን ወድጄው

ሳልመለስ ፊቴን ላላዞር

ወስኛለሁ በእግሩ ሥር መኖር

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

የቀድሞ ታሪኬን ትታችሁ

አውሩት የዛሬውን ባካችሁ

እንዴት እንዳዳነኝ መስክሩ

ይሄ ነው ድንቅና ተዓምሩ

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

መላ ያጣ የተጨነቀ

ተስፋው በምድር ላይ ያለቀ

ይምጣ ምላሽ አለ ኢየሱስ ጋር

አለቀልኝ ያለ የሰጋ

ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ

ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ

አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ

ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ