Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰው እንደፀና

Sew Endetsena

2005 · ትራክ 8 · 6:56 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰው እንደፀና

አይቆይ ሆኖ ገናና

ጉልበቱ ይክደዋል

ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (፪x)

አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም

ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (፪x)

ለውበትህ ወደር የለው (፪x)

በሰማይ በምድር መሳይ የለው (፪x)

ኃይሉ ከሁሉ የበረታ (፪x)

የጌቶች ሁሉ ነው ጌታ (፪x)

ለማንም አለ ሳይረታ (፪x)

ሰው እንደፀና

አይቆይ ሆኖ ገናና

ጉልበቱ ይከብደዋል

ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (፪x)

አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም

ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (፪x)

ብርቱ ኃያላኖች ተነሱ (፪x)

ሞት አይቀርምና ተረሱ (፪x)

እርጅና ድካም የማያውቀው (፪x)

ጥበብ ዕውቀቱ የጠለቀው (፪x)

ባለ ብዙ ክብር እግዚአብሔር ነው (፪x)

ሰው እንደፀና

አይቆይ ሆኖ ገናና

ጉልበቱ ይከብደዋል

ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (፪x)

አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም

ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (፪x)

የተነሱበትን ያዋርዳል (፪x)

ትዕቢተኞችን ይቀጣል (፪x)

የተፈሩትን የማይፈራ (፪x)

ዓይናቸው እያየ አለ እየሰራ (፪x)

እየናደ ግዙፉን ተራራ (፪x)

ሰው እንደፀና

አይቆይ ሆኖ ገናና

ጉልበቱ ይከብደዋል

ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (፪x)

አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም

ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (፪x)

ብቻውን ተዓምራት ያደርጋል (፪x)

ያለ ሠራዊት ይዋጋል (፪x)

በድል ላይ ድልን እያገኘ (፪x)

ጠላቶቹን አዋርዶ እየሸኘ (፪x)

አንድ እርሱ ብቻ ነው የተገኘ (፪x)

ሰው እንደፀና

አይቆይ ሆኖ ገናና

ጉልበቱ ይከብደዋል

ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (፪x)

አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም

ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ