ሞትን የረታ ጌታ
Moten Yereta Gieta
2005 · ትራክ 5 · 5:46 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው
የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው
አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል
አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የዓለም መድኃኒት ይሄን ትሁት
ቢደፋ አንገቱን ቀላል አርገውት
እውር ሲያበራ ዲዳ ሲያናግር
በክፉ አናት ላይ እሳት ሲጭር
ተደንቀው አዩት ኧረ ይሄስ ማነው
አውሎ ንፋሱን ወጀቡን የሚያዘው
አዝማች · Chorus
ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው
የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው
አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል
አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል
ቁጥር 2 · Verse 2
ትክክለኛ ሰራተኛ
ሽንገላ የሌለበት እውነተኛ
ሃሰተኞች ቢያደናብሩ
ቃሉን በተንኮል ቢመነዝሩ
ልቡ አይደነግጥ ምንም ቢሆን አይፈራ
በአደባባይ በግልጥ አለ እየሰራ
አዝማች · Chorus
ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው
የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው
አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል
አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል
ቁጥር 3 · Verse 3
ያንበረከከ መተተኞችን
በሰው ላይ የሚጫወቱ ጠንቋዮችን
ጓዛቸውን ጥለው ፈረጠጡ
በቁጣው ጅራፍ እየተቀጡ
ጌታ ነን ያሉ የታል አቅማቸው
ወድቀው ቀሩ እንጂ ሲነሱ አላየናቸው
አዝማች · Chorus
ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው
የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው
አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል
አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል
ቁጥር 4 · Verse 4
ወረት መስሏቸው የነገራቸው
በሶስተኛው ቀን እነሳለሁ ሲላቸው
መሳቂያ አደረጉት መሳለቂያ
ምን ልታመጣ ከእንግዲህ ወዲያ
የጠበቃት ቀን ደረሰችና
አናወጣቸው ከሞት ተነሳና
አዝማች · Chorus
ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው
የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው
አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል
አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ