Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬ

Amlakie

2005 · ትራክ 3 · 5:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ

ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ

ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ

አቤት ሲችል ሲያውቅበት

አቤት ሲችል ሲያውቅበት

አቤት ሲችል ሲያውቅበት (፪x)

ከቤት ከመንደሩ ከአባቱ ቤት ወጣ

ዘሩን እንደ አሸዋ ሊያበዛለት መጣ

የብዙ ህዝብ አባት በኩር አደረገው

መሃኑን አብረሃም በልጅ ልጅ ባረከው (፫x)

አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ

ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ

ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ

አቤት ሲችል ሲያውቅበት (፫x)

የገዛ ወንድሞቹ ለባዕድ ሰዎች ሸጡት

በህልሙ አንዳች እንዳይሆን አሳልፈው ሰጡት

ነገ ነገን ወልዶ እውነቱ ወጣና

ወድቀው ሰገዱለት ዮሴፍ ተሾመና (፫x)

አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ

ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ

ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ

አቤት ሲችል ሲያውቅበት (፫x)

የበግ ጅራት ሲከተል ግራገሩ እረኛ

ንግሥናውን አያውቅ መሆኑን ተረኛ

ውጣ ውረዱን አልፎ በትሩን በእጁ ሰጠው

እልፍ ገዳይ አምላክ ዙፋን ላይ አስቀመጠው (፫x)

አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ

ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ

ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ

አቤት ሲችል ሲያውቅበት (፫x)

አናብስቶች ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት ቀንተውበት

ከፀሎት ሌላ ምክኒያት ሰበብ አጥተውበት

አልፈቀደላቸውም እንዲቀለጣጥሙት

የዳንኤልን አምላክ ተባለ አምልኩት (፫x)

አምላኬ እንዲህና እንዲያ ያደርጋል ላረፉበትማ

ምንኛ ያስደስታል በማዳን ስልቱማ

ማንም አይደርስበት ሲረዳና ሲያነሳ

አቤት ሲችል ሲያውቅበት (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ