ከወደደ አይለቅም
Kewedede Ayleqem
2005 · ትራክ 9 · 4:31 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ
ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ስራብ እያበላኝ ስጠማ እያጠጣኝ
ጉዴን ገመናዬን እየሸፈነልኝ
ምን ጐደለህ እያለ ሌት ተቀን ያየኛል
የድሃ አደግ አባት እግዚአብሔር ወዶኛል
አዝማች · Chorus
ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ
ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ የማደርገው
ጌታዬና አምላኬ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው
ብድራት ፊቴ አለ የተዘጋጀልኝ
ማንም አይወስደውም ኢየሱስ እያለልኝ
አዝማች · Chorus
ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ
ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዳለፈ ውኃ ችግሬን አስረሳኝ
የማይቻለውን አስችሎ አሳለፈኝ
ሰላሙ በዛልኝ ሃዘኔ ተረስቷል
በእግዚአብሔር በአምላኬ ደስታዬ ጨምሯል
አዝማች · Chorus
ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ
ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከማር ይልቅ ጣፍጦ አየሁት ኑሮዬን
እጅግ አከበርኩት ቸሩ መድኃኒቴን
በለመለመ መስክ ሁሌ ያሰማራኛል
የበረከት አምላክ እግዚአብሔር ባርኮኛል
አዝማች · Chorus
ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ
ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ