ገና ብዙ ክብር
Gena Bezu Keber
2005 · ትራክ 11 · 5:39 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ገና ብዙ (፫x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል
የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል
ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መድኃኒት አለ እናንተ ጋር አድኖ ፈውሶ የሚያስቀር
መንገዱን ባካችሁ አሳዩን ወደ ሕይወት መግቢያውን በር
ይሉናል ይለምኑናል የሚያቁን የምናውቃቸው
ተፀይፈው ያባረሩን ከሰፈር ከመንደራቸው
አዝማች · Chorus
ገና ብዙ (፫x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል
የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል
ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የኃጥያት የችግር ቀንበር ተጭኖ በሰው ሁሉ ላይ
መታወቂያችን ርሃብ ሆነ ተንቀናል ዞሮ እኛን ላይ
የድሆችን ጩኸት ሰምቶ ከሰማይ ትዕዛዝ ያወጣል
ቸነፈር ጉስቁልናውን አባሮት ጥጋብ ይጠራል
አዝማች · Chorus
ገና ብዙ (፫x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል
የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል
ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከኃጥያት ጋር ጨዋታ ይዘው በጊዜያዊ ደስታ ታለው
ክብራቸውን በነውር ሸጠው ፈጣሪያቸውን እረስተው
ገለባ የሚበላ እሳት የመለኮት ኃይል ይመጣል
አስመሳይ አታላይ ሁሉ ለአንዱ ጌታ ክብር ይሰጣል
አዝማች · Chorus
ገና ብዙ (፫x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል
የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል
ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ፅድቁ ሊገለጥ ማዳኑ ቀረበ ከትላንት ዛሬ
የሆታ ቀን ሊመጣ ነው በምድራችን ላይ ዝማሬ
በሥሙ ድንቅና ተዓምር ይሰራል ዝናው ይወጣል
በቤት ጓዳ በአደባባይ ኢየሱስ አዳኝ ነው ይባላል
አዝማች · Chorus
ገና ብዙ (፫x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል
የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል
ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ