በሰማይ እንዳሉ
Besemay Endalu
2005 · ትራክ 6 · 5:10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች
እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች
ይኸው እስከ ዛሬ
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ
ቁጥር 1 · Verse 1
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (፪x)
ሙታን ሳለን ያኔ በደል የተሞላን
ስንወጋው ቁስልህን ኃጥያት እየሰራን
ፍቅርህ በርትቶ ነው ቁጣህን የሻረው
ልበ ቅን ሆነህ ነው ክፉውን የማርከው (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች
እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች
ይኸው እስከ ዛሬ
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተሰበረ ቀንበር ሸክም ተራገፈ
ከእንግዲህ እስር የለም ሁሉ በአንተ አለፈ
ከድካም በረታን ጉልበት አግኝተናል
ኃይልን በምትሰጠን ባለ ድል ሆነናል (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች
እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች
ይኸው እስከ ዛሬ
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከተጠመደብን ወጥመድ አስመለጥከን
መኖሪያ ከለላ መሸሸጊያ ሆንከን
ነጣቂም አይነካን ምን ድፍረት አግኝቶ
ይኸው ምህረትህን አይቶ በእኛ ላይ በዝቶ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች
እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች
ይኸው እስከ ዛሬ
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁሉን ቻይ ትከሻ ስንቱን አዝሎ አኑሯል
የአባትነት ምክርህ ጠማማን አቅንቷል
ምን ያልሆንከው አለ ለመረጥከን ለእኛ
ጉያህ መግባት ቻልን ሆነን እድለኛ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች
እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች
ይኸው እስከ ዛሬ
አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ