ባሕሩ ተከፍሎ ባላይ እንኳን
Baheru Tekeflo Balay Enkuan
2003 · ትራክ 6 · 6:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ባሕሩ ተከፍሎ ባላይ እንኳን
እኔ ግን ከበሮዬን አነሳለሁ (፪x)
ሁኔታው ባይመችም እንኳን
እኔ ግን ለሥምህ እዘምራለሁ
እኔ ግን ለሥምህ እዘምራለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በለቅሶ ሸለቆ በወሰነው ሥፍራ
የሕግ መምህር በዚያ በረከትን (፫x) አዟል
በዚያ በረከትን (፫x) አዟል
በለቅሶ ሸለቆ በወሰነው ሥፍራ
የሕግ መምህር በዚያ በረከትን (፫x) አዟል
በዚያ በረከትን (፫x) አዟል
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኔ ከፍታ
ኢየሱስ ነህ የእኔ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ ከቀስት ፊት ፈጥኜ አመልጥ ዘንድ
በመንገዴ ሁሉ ምልክት አደረግህ
ሥምህን ለሚፈሩ መቼ ዝም ትላለህ
ሁሌም ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ (፪x)
በጠላቴ ፊት እኔን አክብረህ
እንዲህ አምሮብኝ ታኖረኛለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኔ ከፍታ
ኢየሱስ ነህ የእኔ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሞቴን የተመኘ በእኔ ፋንታ ገብቷል
ውርደቴን (ጌታ ለውጠሃል) ጌታ ለውጠሃል (፪x)
አቤቱ በኃይልህ ደስ ይለኛል
በማዳንህ እጅግ ደስ ይለኛል (፪x)
(በበጐ በረከት) በበጐ በረከት ደርሰህልኛል (፬x)
(በቃሉ) በቃሉ የታመነ ያለውን የሚያደርግ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ ቢፈለግ (፪x)
(የለም) የለም የለም የለም አዎ የለም
የለም የለም (ቢፈለግም) ቢፈለግም የለም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ክብርንና ግርማን ለብሰህ (፫x)
ብርሃንን እንደ ልብስ ለብሰህ
አንተ ለዘለዓለም ትኖራለህ (፬x)
ክብርንና ግርማን ለብሰህ (፫x)
ብርሃንን እንደ ልብስ ለብሰህ
አንተ ለዘለዓለም ትኖራለህ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
የእኔ ጌታ አንተን ማን ይስተካከላል
ከፍ ከፍ ካለው በላይ አንተ ከፍ ብለሃል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኔ ከፍታ
ኢየሱስ ነህ የእኔ ንጉሥ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ