Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በከፍታ ከፍ አድርጌ

Bekefeta Kef Adregie Akebrehalehu

2003 · ትራክ 10 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በከፍታ ከፍ አድርጌ አከብርሃለሁ

በሕይወቴ ገዢ አድርጌ እሾምሃለሁ (፪x)

አንተ እግዚአብሔር ነህ

ሥምህ ለእኔ ጋሻ ነው

ልብህ መታመኛዬ

ክንድህ ታዳጊዬ ነው (፪x)

ክንድህ ታዳጊዬ ነው (፬x)

አምላኬ ግሩም ነህ ግሩም

ሥምህ ግሩም ግሩም

አላማህ ግሩም ግሩም

የሚሆንህ አቻ የለም (፪x)

አንተ በዘለዓለም ተራሮች ላይ

ውበትህ እንደ ንጋት የሚታይ

ፍጥረትን አማልሎ አስከተለ

አቤት አቤት ሥራህ ግሩም ነው (፪x)

የሚወራ የሚወራ

እጅ በአፍ ነው የአንተ ሥራ (፪x)

ትውልድ ይናገር ዛሬም ይናገር

ያየ የሰማ ዝናህን ይመስክር

እጅ በአፍ ነው የአንተ ሥራ

ልቤ ሸፈተ ክብርህን ሲያወራ (፪x)

ስወጣም አልሰጋ ስገባም አልሰጋ

ብርቱ አማኑኤል አለ ከእኔ ጋራ (፪x)

ከፊቴ ቀድመህ ትወጣለህ

ጠላቶቼን ትመታለህ (፪x)

ብዙ ኃይልህ ነው በእኔ የተገለጠው

አንዳች ኃይል የለም የሚቋቋመው

የጠላትን ድንበር ጥሶ ይሄዳል

ይገሰግሳል ማን ያቆመዋል

ኦ ማን ያቆመዋል (፫x)

ብዙ ኃይልህ ነው በእኔ የተገለጠው

አንዳች ኃይል የለም የሚቋቋመው

የጠላትን ድንበር ጥሶ ይሄዳል

ይገሰግሳል ማን ያቆመዋል

ኦ ማን ያቆመዋል (፫x)

ስወጣም አልሰጋ ስገባም አልሰጋ

ብርቱ አማኑኤል አለ ከእኔ ጋራ (፪x)

ከፊቴ ቀድመህ ትወጣለህ

ጠላቶቼን ትመታለህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ