የክብርህን ማደሪያ ወደድኩት
Yekebrehen Maderiya Wededkut
2003 · ትራክ 7 · 5:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ የክብርህን ማደሪያ ወደድኩት
አቤቱ የቤትህን ሥራ መረጥኩት (፪x)
አንተ በዚያ ስላለህ
እኔን ታሳርፋለህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር (፪x)
ፍቅር አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ
ፍቅር አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በተከበበ ከተማ ውስጥ
ምህረቱን ምህረቱን ለእኔ አበዛልኝ
አምላኬ እንደ ሰው ስላይደለ
ትላንትን ትላንትን በእርሱ አለፍኩኝ
አምላኬ እንደ ሰው ስላይደለ
ዛሬንም ዛሬንም በእርሱ አለሁኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ ከፍ በል ከፍ ከፍ በል
ሌላማ ሌላም ምን ልበል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከልቤ መልካም ነገር አፍልቀሃል
ሕይወቴ አንተን ብቻ ማምለክ ሆኗል (፫x)
አንተ ድንቅ ነህ ማለት
አንተ ግሩም ነህ ማለትን (፪x)
በሆነልኝ ባልሆነልኝ እንዳደንቅህ
እድል ሰጥተኸኛል እንዳከብርህ (፪x)
እድል ሰጥተኸኛል እንዳነግሥህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ ያላዘዝኸው አንተ ያልፈቀድኸው
ጌታ ያላዘዝኸው አንተ ያልፈቀድኸው
መች ይሆናል አምላኬ ሳታየው (፬x)
ጌታ ያላዘዝኸው አንተ ያልፈቀድኸው
ጌታ ያላዘዝኸው አንተ ያልፈቀድኸው
መች ይሆናል አምላኬ ሳታየው (፬x)
አዝማች · Chorus
ኦ ከፍ በል ከፍ ከፍ በል
ሌላማ ሌላም ምን ልበል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ