Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምላሴ ጽድቅህን ይናገራል

Melasie Tsedqehen Yenageral

2003 · ትራክ 3 · 6:02 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

{ምላሴ ጽድቅህን ይናገራል ፣ አዎ ይናገራል

[አንደበቴ ክብርህን ያወራል] (፬x)} (፪x)

{ ክብርህ ከሰማያት ከፍታ በላይ ነው

ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ያማረ ነው

ምሥጋናህ በምድር ሞልቶ ተትረፍርፎአል

እንዳንተ ገናና ኧረ ከቶ የት አል?] (፪x)

[ ገናና ነህ ገናና] (፬x) } (፪x)

{ ሰማያት የእጆችህን ሥራ ተናገሩ ቢባል

ስለአንተ መተረክ ቢችሉ ስንቱን ባወሩ

እኔ ግን ተአምራቶችህን እናገራለሁ

ፈቅጄ ምሥጋናን ከልቤ እሰጥሃለሁ} (፪x)

{ አንተን የምባርክበት መንፈስህን ሰጥተኸኛል

ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ? ፍቅርህ ሁሌ ያዘምረኛል} (፪x)

{ ምላሴ ጽድቅህን ይናገራል ፣ አዎ ይናገራል

[ አንደበቴ ክብርህን ያወራል] (፬x) } (፪x)

{ የከፍተኛነቴ ሰይፍ የረድኤቴ ጋሻ ነህ

[ በሕያዋን ምድር እድል ፈንታዬ አንተ ነህ] (፬x) } (፪x)

{ ልኡል የሰውን ፍርድ ትመልስ ዘንድ

[ ታማኝ ነህ እህህህ] (፬x) } (፪x)

{ የእኔ ፍርድ ይጣመም ዘንድ

[ አንተ እሺ አትልም ] (፬x) } (፪x)

{ [ ከጥንትም ጀምሮ ከትውልድ ጅማሬ] (፪x)

[ ፍርድህ አልተዛባም ይኸው እስከ ዛሬ ] (፪x) } (፪x)

አቤት ሲያምርብህ ጌታዬ ስትሠራ

አቤት ሲያምርብህ ኢየሱሴ ስትሠራ

አቤት ሲያምርብህ ጌታዬ ስትሠራ

አቤት ሲያምርብህ ኢየሱሴ ስትሠራ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ