Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተራራውን ስትንድ ሸለቆውን ስትሞላ

Terarawen Setened Sheleqowen Setmola

2003 · ትራክ 8 · 6:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተራራውን ስትንድ ፣ ኦሆሆ

ሸለቆው ሲሞላ ፣ አሃሃ (፪x)

ማነው ያልገመተው መኖርህን

አንተ ከእኔ ጋራ አሃሃ

አንተ ከእኔ ጋራ አሃሃ (፪x)

ልቤ አረፈብህ (፪x)

ሥምንም አገኘሁ በአንተ በዳንኩብህ (፪x)

ከታናሹ ጋር ከፍ ባለው ሥፍራ ላይ ትቀመጣለህ

ምሥጋናን ከእርሱ አንተ ትወስዳለህ (፪x)

የምሥጋናዬ መልካሙ መዓዛ

አንተን ያክብርህ ፣ መቅደስህን ይሙላ (፫x)

ከታናሹ ጋር ከፍ ባለው ሥፍራ ላይ ትቀመጣለህ

ምሥጋናን ከእርሱ አንተ ትወስዳለህ (፪x)

የምሥጋናዬ መልካሙ መዓዛ

አንተን ያክብርህ ፣ መቅደስህን ይሙላ (፫x)

አሁንማ የእኔ የምለው አለኝ

አሁንማ ወደ እልፍኙ ገባሁ

አሁንማ እታመነዋለሁ

አሁንማ የልቤን አገኘሁ (፪x)

ተራራውን ስትንድ ፣ ኦሆሆ

ሸለቆው ሲሞላ ፣ አሃሃ (፪x)

ማነው ያልገመተው መኖርህን

አንተ ከእኔ ጋራ አሃሃ

አንተ ከእኔ ጋራ አሃሃ (፪x)

ልቤ አረፈብህ (፪x)

ሥምንም አገኘሁ በአንተ በዳንኩብህ (፪x)

የምድር ፍጥረት አንዱ ባንዳቸው ይደነቃሉ

ዓይኖቼ ግን አንተን ያያሉ (፬x)

የምድር ፍጥረት አንዱ ባንዳቸው ይደነቃሉ

ዓይኖቼ ግን አንተን ያያሉ (፬x)

በራልኝ (፫x)

እኔም አየሁኝ (፪x)

በብርሃንህ ብርሃንን አየሁ (፪x)

ከጨለማ ውስጥ እኔ አምልጫለሁ

እኔ አምልጫለሁ (፪x)

ታላቅ ሁን ዛሬም ታላቅ ሁን

ታላቅ ሁን ሁሌም ታላቅ ሁን (፪x)

አንተ ታላቅ ነህ ሥራህም ታላቅ (፬x)

ታላቅ ሁን ዛሬም ታላቅ ሁን

ታላቅ ሁን ሁሌም ታላቅ ሁን (፪x)

አንተ ታላቅ ነህ ሥራህም ታላቅ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ