በገናናው ዙፋንህ
Begenanaw Zufaneh
2003 · ትራክ 2 · 7:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከገናናው ዙፋንህ
ክብር በሞላበት መቅደስህ
አይሃለሁ ተውበሃል
ክብር ይሁንልህ በማደሪያህ (፪x)
በሰማያት ያለኸው በላይ
ናፍቆቴ የልቤ ርሃብ
ከሞት ወጥመድ ያመለጥኩብህ
ወግ ማዕረግ የቀመስኩብህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንድ ነህ ለእኔ አንድ
ብርቅ ነህ ለእኔ አንድ
ይኸው ምሥጋናዬ የእኔ መደምደሚያ
አንተ ካለህበት ይድረስ ከማደሪያ
ከቅዱስ ማደሪያ አሃ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብርህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ
ውበትህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ
ጥበብህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ
ሥራህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ
አንተ የሁሉ የበላይ
ሥምህ ገነነ በእኔ ላይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቅድስና እና እውነት በመቅደስህ (፪x)
ክብር ታላቅነት የራስህ (፮x)
ቅድስና እና እውነት በመቅደስህ (፪x)
ክብር ታላቅነት የራስህ (፲x)
አዝማች · Chorus
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮች ያለች
አንዲቷ ቀን ለእኔ ትሻላለች (፬x)
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮች ያለች
አንዲቷ ቀን ለእኔ ትሻላለች (፬x)
ጌታዬ ነገሬን እስኪጨርስ ድረስ አያርፍም (፬x)
ያመንኩትን አውቃለሁኝ እና አላፍርም (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ ስለ እርሱ ሳወራ
ሰርቷል ጌታ የእኔን ሥራ (፪x)
እኔ ስለ እርሱ ስናገር
ሰራው ጌታ የእኔን ነገር (፪x)
አዝማች · Chorus
(ያመንኩትን) ያመንኩትን
(አውቃለሁና) አውቃለሁና
(አላፍርም) አላፍርም (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ