ለአላማህ አገኘኸኝ
Lealamah Agegnehegn
2003 · ትራክ 5 · 4:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዓላማ አገኘኸኝ
ለሃሳብህ ለየኸኝ
ደነቀኝ የአንተ ምርጫ
አዝማች · Chorus
ጥሪህን በእኔ ላይ አጸናህ (፪x)
እንዳስለመድኸኝ ዛሬ አንተን ማመሥገን
በልቤ ሞልቷል ለማድነቅ አንተን (፪x)
አንተን ለማድነቅ አንተን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ የልጅነት የልቤ ወዳጄ
ፍቅርህን አስባለሁ ጐህ ሲቀድ ማልጄ
ተነሽ ቢለኝ ነቃሁ ይሄ ትዝታዬ
ውለታህን አስቆጠረኝ ላመሥግን በተራዬ
ተነስ ቢለኝ ነቃሁ ይሄ ትዝታዬ
ውለታህን አስቆጠረኝ ላመሥግን በተራዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የእኔ ጌታ መልካም በማድረጉ
ደስ ይለዋል ለእኔ ለልጁ (፪x)
በሰማይ በምድር
እንዳንተ የሚሆን አልተገኘልህም (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሉያ ፣ ሉያ ፣ ሉያ (፬x)
የእጆችህ ሥራ ጽድቅና እውነት ነው
በእውነትና በቅን የተሠራ ነው
ስለዚህ ምሥጋናን ብጨምር ባበዛ
ሳነሳሳ ብውል ሥራህን ባወራ (፪x)
ብዙ ነው በጣም ብዙ ነው
ብዙ ነው እጅግ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚያስገርም አንድ ነገር ሰማሁ
ውበትህ ስላስደመመኝ ይህን ውዴን አየሁ (፪x)
ለካስ የእራሴ ወዳጅ ነው
ምድርን ያስደነቀው
አስገራሚው የእራሴ ጌታ ነው
ምድርን ጉድ ያሰኘው (፪x)
ጉድ ያሰኘው
ምድርን ጉድ ያሰኘው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ