Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማዳኑ ከማዕበሉ ፈጥኗል

Madanu Kemaebelu Fetnual

2003 · ትራክ 1 · 6:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መርከቤ ከውሃው በላይ

ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ብሏል

ማዳኑ ከማዕበሉ ፈጥኗል

መጨነቅ ከእንግዲህ አብቅቷል (፪x)

እያለ ጌታ መርከቡ ላይ

የምን ሥጋት ነው ወጀብ ቢታይ

እያለ ጐኔ የሚያኮራ

በጣር ሰዓትም የሚጠራ (፪x)

የፈጠነ ቢመስል ወጀብ ማእበሉ

ነፋሳት በአንድ ላይ ተባብረው ቢያይሉ

ተስፋ እንደሌለው ሰው ምድር ብትረዳቸው

ኢየሱስ እኮ ነው የበላያቸው (፪x)

አልፈራም እኔ አልፈራም (፮x)

እያለ ጌታ መርከቡ ላይ

የምን ሥጋት ነው ወጀብ ቢታይ

እያለ ጐኔ የሚያኮራ

በጣር ሰዓትም የሚጠራ (፪x)

(ከግቤ እደርሳለሁ) ከግቤ እደርሳለሁ

ከባሕሩ ዳርቻ

(እንቁዬን አልጥልም) እንቁዬን አልጥልም

አይደለሁ ለብቻ (፬x)

(ያሰጠመኝ መስሎት) ያሰጠመኝ መስሎት

ማእበሉ ሲያፏጭ

(እኔ ግን አመለጥኩ) እኔ ግን አመለጥኩ

ጠላቴን በአቋራጭ (፬x)

(መርከቤ) መርከቤ ከውሃው በላይ

(ከፍ ከፍ) ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ብሏል

(ማዳኑ) ማዳኑ ከማእበሉ ፈጥኗል

(መጨነቅ) መጨነቅ ከእንግዲህ አብቅቷል (፪x)

(እያለ ጌታ) እያለ ጌታ

(መርከቡ ላይ) መርከቡ ላይ

(የምን ሥጋት ነው) የምን ሥጋት ነው

(ወጀብ ቢታይ) ወጀብ ቢታይ

(እያለ ጐኔ) እያለ ጐኔ የሚያኮራ

(በጣር ሰዓት) በጣር ሰዓት

(የሚጠራ) የሚጠራ (፪x)

አልፈራም እኔ አልፈራም (፴፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ