ትላንት አንተ ነበርክ ያለህ
Telant Ante Neberk Yaleh
2003 · ትራክ 4 · 5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ትናንት አንተ ነበርክ ያለኸኝ
ዛሬም አንድ አንተ ነህ ያለኸኝ (፪x)
የልቤንም ሁሉ አንድ ላይ ጠቅልዬ
ተባረክ እላለሁ ክብር ይሁንልህ ብዬ
ክብር ይሁንልህ ብዬ (፪x)
ሌላማ ለአንተ ምንስ ይባላል
ከልብ ከሆነ ይሄ ይበቃሃል
ይሄ ይበቃሃል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከእናት ከአባት በላይ አንተ ለእኔ ሆነኸኛል
ገና ከልጅነቴ ጠብቀህ አሳድገኸኛል
ከሗላ ከፊቴ ዙሪያዬን ቅጥር ቀጥረሃል
ጠላቴ ከአንተ አልፎ መች እኔን ይነካኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ትናንት አንተ ነበርክ ያለኸኝ
ዛሬም አንድ አንተ ነህ ያለኸኝ (፪x)
የልቤንም ሁሉ አንድ ላይ ጠቅልዬ
ተባረክ እላለሁ ክብር ይሁንልህ ብዬ
ክብር ይሁንልህ ብዬ (፪x)
ሌላማ ለአንተ ምንስ ይባላል
ከልብ ከሆነ ይሄ ይበቃሃል
ይሄ ይበቃሃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ያልከው ሁሉ ሁሉ ሆነ
ከሆነው ሁሉ የለ ያልሆነ (፪x)
ምድርን እንኳን ፈጥሯል ቃልህ
ማን በአንተ ሰጠው ሊጠረጥርህ
ምድርን እንኳን ፈጥሯል ቃልህ
ማን በአንተ ሰጠው ሊጠረጥርህ (፪x)
ባሕርን ከፍሎ ሕዝቡን መራ
ተባለልህ ትላንት ድንቅ ሥራ
ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለህ
አቀረብኸኝ ወደ ራስህ እርቅን ፈጥረህ (፪x)
ባሕርን ከፍሎ ሕዝቡን መራ
ተባለልህ ትላንት ድንቅ ሥራ
ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለህ
አቀረብኸኝ ወደ ራስህ እርቅን ፈጥረህ (፪x)
ኧረ ጌታ ልዩ ነህ
ምህረትህ በዛልኝ (፬x)
ኧረ ጌታ ልዩ ነህ
ምህረትህ በዛልኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ