Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምህረትህ

Mehereteh

2003 · ትራክ 9 · 5:30 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምህረትህን ትውልድ ይናገራል

ልቤስ ቢሆን ኧረ መች ረስቶሃል

ያደረግኸው አልቀረ እንደ ዋዛ

ልዝረፍልህ ቅኔን እያበዛሁ (፪x)

አንተኑ ብዬ ላምልክህ አላማዬ

ከደጅህ መጣሁ ምሥጋናን ተሸክሜ (፪x)

ምን አሃሃሃ ሃሃ እልሃለሁ

እንከን አይወጣው ሥራህ ግሩም ነው

አንዳች ሳላወራ እንዲህ ነው ሳልለው

ሥራህ ምስክር ነው (፪x)

ሕያው ነህ ለዘለዓለም (፪x) ሕያው

ሕያው ነህ ለዘለዓለም

ሕያው ነህ ለዘለዓለም

እንደ አንተ አላየሁም በፍቅርህ ብዛት

ሁሉንም የሚወድ አይነካካው ወረት

ይገርማል

በምድር ዙሪያ ሥምህ ይጠራ

አቻ የለህም ሆነህ ገናና (፪x)

እንዳንተ አላየሁም በፍቅርህ ብዛት

ሁሉንም የሚወድ አይነካካው ወረት

ይገርማል

በምድር ዙሪያ ሥምህ ይጠራ

አቻ የለህም ሆነህ ገናና (፪x)

በምን አንደበት እንዴት ይወራ

የትኛው ቀርቶ የቱ ይጠራ

ሥራህ ብዙ ነው የመድሃኒቴ

በልቤ አምላክ ጸና ጉልበቴ (፪x)

ልቤ ጸና (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ