Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በድል በድል

Bedel Bedel

2014 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በድል በድል (፪x)

እያሳለፈኝ ቆምኩ በተዓምር

እያስመለጠኝ በቸርነቱ

ያዘምረኛል ይህ ቸር አቤቱ (፪x)

አቤቱ አቤቱ በዛ ቸርነቱ (፬x)

ጠላቶች በእኔ ላይ ሲማማሉ

የሚረዳው የታል ሲሉ (፪x)

ረዳቴ ከሰማይ ወረደልኝ

አለሁልህ ልጄ እያለኝ

አለሁልህ ልጄ እያለኝ (፪x)

በፍቅርህ ብዛት በቸርነትህ

እኔስ አለፍኩኝ በአባትነትህ

ለነገ ደግሞ ዋስትናዬ ነህ

ስጋት አይገባኝ ጌታዬ በአንተ (፪x)

በድል በድል (፪x)

እያሳለፈኝ ቆምኩ በተዓምር

እያስመለጠኝ በቸርነቱ

ያዘምረኛል ይህ ቸር አቤቱ (፪x)

አቤቱ አቤቱ በዛ ቸርነቱ (፬x)

ከአስፈሪው መንገዴ ታደከኝ

በእጆችህ ይዘኸኝ (፪x)

ወጥመድ ተሰበረ አመለጥኩኝ

በእጆችህ ይዘኸኝ

በእጆችህ ይዘኸኝ (፪x)

በፍቅርህ ብዛት በቸርነትህ

እኔስ አለፍኩኝ በአባትነትህ

ለነገ ደግሞ ዋስትናዬ ነህ

ስጋት አይገባኝ ጌታዬ በአንተ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ