Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይሁን ሆይ

Yehun Hoy

2014 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ይሁን ሆይ (፪x)

ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ

የእኔ መንገድ የሚያምረው

አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው (፪x)

አንተ የሌለህበት ብራብ ላያጠግበኝ

መንገዴም ላይቀና ሕይወት ላይሆንልኝ

ልጠይቅ ፈቃድህን አባቴ ነህና

እሾህ ማይኖረው መንገዴ ሲቀና (፪x)

አሃሃ በጐ መስሎኝ ፤ አሃሃ በዓይኔ አይቼ

አሃሃ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ውስጥ ገብቼ

አሃሃ ያየህልኝን ፤ አሃሃ እንድወርሰው

አሃሃ ምራኝ ጌታ ፤ አሃሃ እንድደርሰው (፪x)

ይሁን ሆይ (፪x)

ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ

የእኔ መንገድ የሚያምረው

አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው (፪x)

በሕይወቴ ስጓዝ ባለፉት ዘመናት

ራሴን ሰምቼ ወጣሁኝ ለጥፋት

ያኔ ይበቃኛል የሳትኩት መንገዴ

ምራኝ እንደቃልህ በአንተ ይሁን ውዴ (፪x)

አሃሃ በጐ መስሎኝ ፤ አሃሃ በዓይኔ አይቼ

አሃሃ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ውስጥ ገብቼ

አሃሃ ያየህልኝን ፤ አሃሃ እንድወርሰው

አሃሃ ምራኝ ጌታ ፤ አሃሃ እንድደርሰው (፪x)

የእኔ መንገድ የሚያምረው

አንተ ቀድመህ ጌታዬ ስትመራኝ ነው

ይሁን ሆይ (፪x)

ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ

የእኔ መንገድ የሚያምረው

አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ