ከአንተ ወዴት
Kante Wediet
2014 · አማርኛ
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
አንተ ዘንድ ቃል አለ
ከአንተ ዘንድ ሕይወት አለ (፪x)
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
አንተ ዘንድ ቃል አለ
ከአንተ ዘንድ ሕይወት አለ (፪x)
ከአንተ ዘንድ የበላ ከአንተ ዘንድ የጠጣ
መቼም አይራብም መቼም አይጠማ
የሕይወት ውኃ ነህ የሕይወት ምንጭ
እረክቶ ይኖራል ጌታ ከአንተ እጅ (፪x)
አንተ ዘንድ ቃል አለ
ከአንተ ዘንድ ሕይወት አለ (፪x)
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
ጌታዬ ከአንተ ወዴት እኔ እሄዳለሁ
አንተ ዘንድ ቃል አለ
ከአንተ ዘንድ ሕይወት አለ (፪x)
መድኃኒቴ ብዬ/እያልኩ እኔ እጣራለሁ
ሕይወት በአንተ ብቻ እኔስ አግኝቻለሁ
ከቶ አልሻም እና ከአንተ ወዲያ ለእኔ
አንተ ብቻ ግዛኝ ቀሪውን ዘመኔ (፪x)
አንተ ዘንድ ቃል አለ
ከአንተ ዘንድ ሕይወት አለ (፪x)
የሕይወት ምንጭ ነህ የሕይወት ምንጭ (፬x)
የሕይወት ምንጭ ነህ የሕይወት ምንጭ (፬x)
መድሃኒቴ እያልኩ እኔ እጣራለሁ
ሕይወት በአንተ ብቻ እኔስ አግኝቻለሁ (፪x)
የሕይወት ምንጭ ነህ የሕይወት ምንጭ (፬x
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ