Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልሰዋ ምሥጋና

Lesewa Mesgana

2014 · ትራክ 11 · 6:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከልብ የሆነ ምሥጋናዬን

ልሰዋ በፊትህ ጌታዬ

ከልብ የሆነ አምልኮዬን

ልሰዋ በፊትህ ጌታዬ

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ ምሥጋናዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ አምልኮዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ ምሥጋናዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ አምልኮዬን

ልሰዋ ምሥጋናዬን ልሰዋ አምልኮዬን (፪x)

ሁኔታን አይቼ በገና አላነሳም

ሞላ አልሞላም ብዪ አምልኮ አልቀንስም

የለት ነው ተግባሬ ስምህን ማወደስ

ጌታ አንተ ስትከብር ይለኛል ደስ ደስ (፪x)

ምሥጋናን ሚሰዋ ስምህን ያከብረዋል

ማዳንህን ደግሞ በምሥጋናው ያወራል (፪x)

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ ምሥጋናዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ አምልኮዬን

ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም ይዘሃል

በሰማዩ ስፍራ በክብር ተቀምጠሃል

ፍጥረት ይስገድልህ ፍጥረት ያመስግንህ

መላዕክት ለስምህ ለክብርህ ይስገዱልህ (፪x)

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ ምሥጋናዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ አምልኮዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ ምሥጋናዬን

ልሰዋልህ (፪x) ልሰዋ አምልኮዬን

ልሰዋ ምሥጋናዬን ልሰዋ አምልኮዬን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ