Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በላይ ነው ቤቴ

Belay New Bietie

2003 · ትራክ 6 · 4:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እወርሳለሁ (፫x) ሃገሬን እወርሳለሁ

አያለሁ (፫x) አምላኬን አያለሁ

እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን

ደርሼ አያለሁ አምላኬን

በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ

አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ

አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ

አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (፪x)

በጉዞ ላይ እያለሁ ብደናቀፍም

ችግርም መከራ ቢፈራረቅም

አንድ ቀን ይሄ ሁሉ ይቀርና

እኔም እሰዋለሁ ለአምላኬ ምሥጋና

አዜማለሁ ሁሌም አዜማለሁ

አዜማለሁ ለጌታ አዜማለሁ (፪x)

እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን

ደርሼ አያለሁ አምላኬን

በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ

አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ

አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ

አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (፪x)

ተስፋ አስቆራጭ ነገር በአቋራጭ ቢነሳም

እምነቴን ሊያስጥል በብርቱ ቢዋጋም

ኢየሱስ ከጐኔ ነው ፍፁም ላይለየኝ

ቃል ገብቶልኛል ጽዮንን ሊያወርሰኝ

ሊያወርሰኝ ጌታ ሊያወርሰኝ

ሊያወርሰኝ ኢየሱስ ሊያወርሰኝ (፪x)

እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን

ደርሼ አያለሁ አምላኬን

በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ

አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ

አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ

አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (፪x)

ጠላት ተስፋ ቁረጥ እኔ አምልጫለሁ

ከዚህ ዓለም ሲቃ በኢየሱስ ድኛለሁ

ጌታዬ ሲመጣ ሄዳለሁ አብሬ

ዘለዓለም እኖራለሁ በሰማይ ሃገሬ

በላይ ነው ቤቴ በላይ ነው

ሰማይ ነው ሃገሬ ሰማይ ነው (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ