በእውነት ለሚወዱህ
Bewnet Lemiweduh
2003 · ትራክ 7 · 4:43 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (፰x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መገፋት መሰደዴ ወደ ግብጽም መውረዴ
ወዶኝ ነው ያደረገው አላማ በእኔ ስላለው
ወጣሁ ቀኑ ደርሶ የበላይ አደረገኝ
ተሾምኩኝ ተመረጥኩኝ ሁሉ ለበጐ ሆነልኝ (፪x)
ሁሉ ለበጐ ሆነልኝ (፬x)
አዝማች · Chorus
በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃዘን ሆነ መቸገሬ ኋላ ግን ሆነ ለክብሬ
አለፍኩት እንደዋዛ መከራዬ ረግፎ እንደጤዛ
ኑሮዬን እንዲህ አጣፍጦ ዘመርኩኝ ሁሉ ተረስቶ
ሆነልኝ ሁሉ ለበጐ ጌታ ነገሬን ውብ አድርጐ (፪x)
ጌታ ነገሬን ውብ አድርጐ (፬x)
አዝማች · Chorus
በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አይበቃም እዘምራለሁ ለአምላኬ እኔ እቀኛለሁ
አምሮልኝ ሁሉ ውብ ሆኗል መከራዬ ድልድይ ሆኖኛል
ተሻገርኩ ሁሉን አልፌ አለሁኝ ከሞት ተርፌ
አይቶልኝ እዚህ አድርሶኛል አክብሮ ያዘምረኛል (፪x)
አክብሮ ያዘምረኛል (፬x)
አዝማች · Chorus
በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ