ለእኔስ የደላኝ
Lenies Yedelagn
2003 · ትራክ 12 · 5:58 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ
በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ
በአንተ የታደለ የተመቸው
እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔስ የደላኝ የተመቸኝ
እፎይ ያልኩበት ያሳረፈኝ
እንደርሱ ማነው የሚደላ
የሚመች የለም ከእርሱ ሌላ
እርሱ ብቻ ነው የሆነኝ ከለላ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ
በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ
በአንተ የታደለ የተመቸው
እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው
ቁጥር 2 · Verse 2
የምመካበት መመኪያዬ
ምታመንበት መታመኚያዬ
የምኮራበት ጽኑ ጋሻዬ
ኢየሱሴ ነው ማረፊያዬ
ታድያለሁ ሆኖኛል ጥላዬ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ
በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ
በአንተ የታደለ የተመቸው
እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ጋሻ የሆነኝ ጽኑ መከታ
ጉልበቴ እርሱ ነው እንዳልረታ
በአንዳች አልሰጋም አልጨነቅም
ሥጋቴን ወስዷል ሥጋት አላውቅም
እፎይ ብያለሁ በመድሃኒያለም
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ
በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ
በአንተ የታደለ የተመቸው
እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ