ተንስ አንተ ትውልድ
Tenes Ante Tewled
2003 · ትራክ 13 · 4:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በውስጥህ እሳቴን አቀጣጥላለሁ
የኃጢአትንም ዱር ጫካን እገልጣለሁ
ነበልባሉ አይጠፋም ይነዳል ጨምሮ
ሰሜኑን ይበላል ከደቡብ ጀምሮ
ነውረኛውን ነገር ፈጽሞ እስኪያጠፋ
የነበልባሉን ኃይል ማነው የሚያጠፋ
ብቻ አንተ ተቀደስ ከነውር ተለይ
ክብሬ በአንተ ላይ ነው ሊገለጥ ሊታይ
አዝማች · Chorus
ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (፪x)
እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ
ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ
ጫማህን አጥልቅ ተነስ
አንተ ተውልድ ተነስ
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ስራ አለኝ በአንተ የምሰራው
በመጀመሪያ ግን ቤቴን ነው ማጠራው
እንዳትሆንብኝ ጥፋት ከሚያገኘው
ዛሬ ቀን እያለ ተጠንቀቅ እልሃለሁ
ይሄን ድምጼን ሰምተህ ቢቀናህ መንገድህ
በምሰራበት ቀን ገንዘብ ትሆናለህ
ሰባራውን ጠጋኝ አጋዥ ትባላለህ
ድል ነሺ በመሆን ደግሞም ትከብራለህ
አዝማች · Chorus
ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (፪x)
እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ
ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ
ጫማህን አጥልቅ ተነስ
አንተ ተውልድ ተነስ
ቁጥር 3 · Verse 3
የተጠራህበት ጥሪ ይህ ነውና
ስራዬን ልትሰራ ጊዜው ቀርቧልና
ቃሌን በደምብ ብላ በአግባቡ ጸልይ
ሃሳቤ ይፈጸማል ያለው በሰማይ
በምድር አምባሳደር ተወካዬ አንተ ነህ
ስራዬን ለመስራት ከልብ ከተሰጠህ
መጨረሻው ደርሷል የምገለጥበት
ለሁሉም እንደስራው ዋጋ ምከፍልበት
አዝማች · Chorus
ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (፪x)
እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ
ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ
ጫማህን አጥልቅ ተነስ
አንተ ተውልድ ተነስ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ