መክበሬ በአንተ ነው
Mekberie Bante New
2003 · ትራክ 9 · 3:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መክበሬ በአንተ ነው እንዲህ መዘመሬ
ከፍታ ላይ ወጣሁ ጸንቶ ቆሟል እግሬ (፪x)
ቅባቱን ለቆብኝ በእኔ ከከበረ
ገና እዘምራለሁ ጠላቴ ሆይ ስማ
ቅባቱ በእኔ ላይ አለው ልዩ አላማ (፪x)
አለው ልዩ አላማ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት (፫x) አቤት (፪x)
የአምላኬ ድንቅ ስራው
ይገርመኛል ይደንቀኛል
እንዲህ ማክበሩ ይገርመኛል
ማሳመሩ ይደንቀኛል
እኔን መምረጡ ይገርመኛል
ሰው ማድረጉ ይገርመኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
ታናሽነቴን አይተህ ሳትንቀኝ
ከማህጸን ሳልወጣ አንተ የለየኸኝ ጌታ የለየኸኝ
ገሃድ አወጣኸኝ ነገር አለ በእኔ
ይገለጥ ክብርህ ቅባቱ ይጨምር
የምትሰራው በእኔ (፪x)
የምትሰራው በእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት (፫x) አቤት (፪x)
የአምላኬ ድንቅ ስራው
ይገርመኛል ይደንቀኛል
እንዲህ ማክበሩ ይገርመኛል
ማሳመሩ ይደንቀኛል
እኔን መምረጡ ይገርመኛል
ሰው ማድረጉ ይገርመኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ከመረጥከኝ ልጅህ ካደረከኝ
በሰጠኸኝ ፀጋ ታማኝ ሰው አድርገኝ (፪x)
ይህ ገና ጅምር ነው አለ ገና ገና
እወርሳለሁ (፪x) እወርሳለሁ ገና (፪x)
እወርሳለሁ ገና (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት (፫x) አቤት (፪x)
የአምላኬ ድንቅ ስራው
ይገርመኛል ይደንቀኛል
እንዲህ ማክበሩ ይገርመኛል
ማሳመሩ ይደንቀኛል
እኔን መምረጡ ይገርመኛል
ሰው ማድረጉ ይገርመኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ