ከቁጥር በዛ
Kequter Beza
2003 · ትራክ 2 · 5:45 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንዴት ተደርጐ ይወራል
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ ጌታዬ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ አባባ
ከቁጥር በዛ ስራህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ስራህ ግሩምና ድንቅ ነው
ባወራው ብናገር አልጨርሰው
ለእኔ ያደረከው እጅግ ብዙ
እንዴት ብዬ ላውራው ስራህ ብዙ (፫x)
አዝማች · Chorus
እንዴት ተደርጐ ይወራል
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ ጌታዬ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ አባባ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ቁጥር 2 · Verse 2
የተደረገልኝ የሆነልኝ
ከአይምሮ በላይ ነው የሰራልኝ
ብዙ ተደርጐልኝ አይቻለሁ
ልናገረው ቃላት አጥቻለው
እንዲያው ተመስገን እላለሁ
አዝማች · Chorus
እንዴት ተደርጐ ይወራል
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ ጌታዬ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ አባባ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንደበቴን ልክፈት ልናገረው
ላሰማ ስራህን ልተርከው
ከቁጥር በላይ ነው የአንተ ስራ
እንዴትስ አድርጌ እንዴት ላውራ
አስገረመኝ የአንተ ስራ
አዝማች · Chorus
እንዴት ተደርጐ ይወራል
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ ጌታዬ
ከቁጥር በዛ ስራህ
ከቁጥር በዛ ስራህ አባባ
ከቁጥር በዛ ስራህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ