Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በማደሪያህ

Bemaderiyah

ትራክ 6 · 5:53 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በማደሪያህ በዙፋንህ ላይ

የእኔ ጌታ ተቀምጠህ የለ ወይ (፪x)

አንተ እያለህ የእኔ አባት

እንዴት ይገባል ልቤ ስጋት (፪x)

በመንገዴ ቅጥርን ቀጥሮ

አታልፈውም ይህን ከቶ

ብሎ ያለው ያ ተራራ

ስፍራን ለቋል ስምህን ስጠራ (፪x)

አንተ እያለህ የእኔ አባት

እንዴት ይገባል ልቤ ሥጋት (፪x)

ሰማይ የአንተ ዙፋንህ

ምድር የአግርህ መርገጫ

ከማንስ ጋር ላስተያይህ

አንተ የለህም እኩያ (፪x)

እኩያ አይገኝለህም (፲፪x)

አንዱ ለአንዱ ቅድስናህን ሲያወሩ

በምሥጋናቸው ማደሪያህን የሞሉ (፪x)

እኔ ስላለኝ ምሥጋና ፤ ይዤ ተነሳሁኝና

ዙፋንህ ስር መጣሁኝ ልሰዋ ፤ ዛሬም እንደገና

ቢወጣልኝ ኖሮ እንዲህ አመስግኜ (፪x)

በሰጠሁህ ነበር አንድ ቃል ጠቅልዬ (፪x)

ግን እንደው ስራህን ስላየሁ በዐይኔ

ተመስገን ስልህ ባሰብኝ እኔ (፪x)

የቱ ተቀንሶ የቱ ይጨመራል (፪x)

አንተ ያረክልኝ ስንቱ ይቆጠራል (፪x)

ዛሬም ተነሳሁ ልዘምር (፪x)

በክብር ላይ ክብር ልጨምር (፬x)

ክብርህን ማውራት አሃ እንዴት ደስ ይላል (፪x)

ስራህን ብናገር አሃ እንዴት ደስ ይላል (፪x)

ክብርህን ማውራት አሃ እንዴት ደስ ይላል (፪x)

ስራህን ብናገር አሃ እንዴት ደስ ይላል (፪x)

ኦሆ ቢዘመርልህ ኦሆ ፤ ኧረ አንተ ሲያንስህ

ኦሆ ቢሰገድልህም ኦሆ ፤ ኧረ አንተ ሲያንስህ (፪x)

ኦሆ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ